ወገናዊነት ለምንጩ / SIDE the Source

27 Mar

ሕብረ፥ቅላጼ ምን ማለት ነው?

ሕይወት ማለትም ሕልውና በአራት ዋና ዋና መስኮች ትገለጻለች፣ ትስተጋበራለች።
1ኛ/ በማህበራዊ መስክ፣ 2ኛ/ በባህላዊ መስክ፣ 3ኛ/ በቁስ፥አካላዊ መስክና፣ 4ኛ/ በመንፈሳዊ መስክ።
እነዚህ መስኮች የየራሳቸው ዓቢይ መድረሻ ግብ፣ የሚጓጉላቸውና የሚስቧቸው ቁም፥ነገሮች አሏቸው።
1ኛ/ ማህበራዊ መስክ ለሰላም፣ 2ኛ/ ባህላዊ መስክ ለሰብዓዊ ባህል ፣ 3ኛ/ ቁስ፥አካላዊ መስክ ለብልጽግና፣ እንዲሁም 4ኛ/ መንፈሳዊ መስክ ለዕምነት፣ ለረቀቀ ዕምነት።
ለእነዚህ መድረሻ ግቦች የሰው፥ልጅ የሚደክመው፣ ለየራስ ቁም ነገርነታቸው ብቻ ሳይሆን፣ የኋላ ኋላ ትውልድ ትውልድን ሲተካ በሚያስመዘግበው የዕድገትና የርቀት ጉዞው፣ 1ኛ/ ቤተ፥ሰላሙን ለማግኘት፣ 2ኛ/ ሙሉ ሰብዓዊ ነጻነት ለመቀናጀት፣ 3ኛ/ ወደ ፍጹማዊነት የሚያመራ ሳይንሳዊ ዕውቀት ላይ ለመድረስ፣ እና እንዲሁም 4ኛ/ በመሎኮታዊ ጥበብ ለመካን ይችል ዘንድ ነው። ሕብረ፥ቅላጼ፣ እነዚህን በሙሉ ይመለከታል።

ሕብረ፥ቅላጼ፣ እነዚህን ቁም፥ነገሮችንና መድረሻ፥ግቦችን በየገጽታቸውና በህብራዊነታቸው ሊስተጋበሩና ሊቀናጁ የሚችሉበትን ሕይወት፣ በረቀቀ አእምሮ ማስተናገድ፣ ማሳናድትና መፍጠር ማለት ነው።

ወገናዊነት ለምንጩ / SIDE the Source

Joomag Digtal

ሕብረ፥ቅላጼ / SIDE SIDE the Source-The Harmony Model

ይህ ሕብረ፥ቅላጼ ሲመረመር ምንድን ነው?

 

 ወገናዊነት ለምንጩ / SIDE the Source/Scribd/

Leave a comment